• Call Us
  • +251..........

ፋይዳ 9.6 ትሪሊዮን ብር በዲጂታል ግብይት እንዲዘዋወር አግዟል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ፋይዳ 9.6 ትሪሊዮን ብር በዲጂታል ግብይት እንዲዘዋወር አግዟል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የአይዲ ፎር አፍሪካ 2025 ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤን በይፋ አስጀምረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት፤ በዲጂታል ዓለም ውስጥ ስንኖር የዲጂታል ማንነት መለያ መጠቀም ለግለሰቦች አቅምን ለሀገራት ጠንካራና ሁሉን አካታች መዋቅር እንዲኖራቸው ያግዛል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
 
ዲጂታል ማንነት የዓለምን ትኩረት እየሳበ በመጣበት ወቅት፣ የዲጂታል ማንነት ውጤታማነትን መለካት የሚቻለው የሰዎችን ህይወት በምን ደረጃ ለውጧል የሚለውን በመለካት ነው ብለዋል፡፡  

ለዓመታት የኢትዮጵያ የማንነት መታወቂያ በተበታተነ መልኩ ሲተገበር መቆየቱን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አሰራሩ ሚሊዮኖችን ከኋላ በዘነጋ መልኩ የተወሰነ የማህበረሰብ ክፍሎች ብቻ ይገለገሉበት እንደነበር ገልፀዋል፡፡ 

ሚሊዮኖች ችግር በሚያገጥማቸው ወቅት መሰረታዊ አገልግሎቶችን ለመስጠት አስቸጋሪ አድርጎት መቆየቱንም ጠቅሰዋል፡፡

ይህን ተከትሎ ከተጭበረበረ ማንነት የፀዳና ተማኝነት ያለው ዲጂታል ማንነትን የሚገልጽ አሰራር ለመፍጠር የፋይዳ ዲጂታል ሲስተምን መዝርጋት እንዳስፈለገ ተናግረዋል፡፡ 
 
ፋይዳ ካርድ ብቻ አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ የግለሰቦችን ግላዊ መረጃዎች ምሥጢራዊነት በመጠበቅ እና አስፈላጊ የሆነውን ብቻ በማጋራት ማንነትን የሚያረጋግጥ ልዩ መለያ ቁጥር መሆኑን ገልጸዋል።

እንደ ፋይናንስ፣ ጤና እና ትምህርት ባሉ ቁልፍ ዘርፎች የተቀናጀው ፋይዳ፣ 9.6 ትሪሊዮን ብር በዲጂታል ግብይት እንዲዘዋወር እያገዘ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስተዋል፡፡ 

ኦንደ ኢቢሲ ዘገባ በኢትዮጵያ 90 ሚሊዮን ሰዎችን ለፋይዳ ለመመዝገብ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑንና እስካሁን ከ15 ሚሊዮን በላይ ሰዎች መመዝገባቸውንም አመልክተዋል።