የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ክልላዊ መድረክ እየተካሄደ ነዉ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ክልላዊ መድረክ ርዕሰ መስተዳደር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት በወላይታ ሶዶ እየተካሄደ ይገኛል ።
'' የመሃሉ ዘመንን መረዳት 'በሚል ሃሳብ እየተካሄደ ባለው በዚሁ መድረክ፦ የክልሉ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ገብረመስቀል ጨላን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ይገኙበታል ።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ጥላሁን ከበደ በዚህ ወቅት ፦ባለፉት ሰባት የለውጡ አመታት በክልሉ ብሎም በሀገሪቱ የተመዘገቡ ስኬቶችን በቀጣይም በዘላቂነት ለማስቀጠል እንደሆነ አስታውቋል ።
መድረኩ በተለይ፦ የህዝብን አንድነት በማጠናከርና ያሉት ፈተናዎች ወደ ድል በመቀየር የሚፈለገውን ብልጽግና ለማረጋገጥ እንደሆነም ነዉ ርዕሰ መስተዳድሩ የገለፁት ።
የተመዘገቡት ስኬቶችን የበለጠ ዉጤታማ ለማድረግ አመራሩ ይበልጥ እንዲዘጋጁ የሚያስችል መድረክ መሆኑን አቶ ጥላሁን ጥላሁን ከበደ አስረድተዋል ።
በመድረኩ "የመሐሉ ዘመን" በሚል ሃሳብ የተዘጋጀ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል።
Copyrights 2021. . All Rights Reserved.
Developed by NATNAEL ABATE