በክልሉ ለአልሚ ባለሀብቶች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል -አቶ ጥላሁን ከበደ
ሚያዝያ 28/2017 ዓ.ም
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለአልሚ ባለሀብቶች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ጥላሁን ከበደ አስታውቋል ።
በክልሉ የኢንቨስትመንት ልማት ለማነቃቃት ያለመ የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል ።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ጥላሁን ከበደ በዚህ ወቅት ፦ክልሉ ከተደራጀበት ጊዜ ጀምሮ የብልጽግና ተምሳሌት ራዕን እዉን ለማድረግ እየተሰራ ነዉ ብለዋል።
በዚህም በክልሉ ያሉ የተፈጥሮ ፀጋዎች እንደ ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም የሚፈለገውን ዉጤት ለማስመዝገብ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል ።
የሀገራችን ችግር ድህነት ነዉ ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ፣ለዚህም አልሚ ባለሀብቶች በሀገሪቱ እንቨስት በማድረግ የሚፈለገውን ብልጽግና ማረጋገጥ እንዳለበት ገልጸዋል ።
በተለይ የውጪ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት ባለሀብቶች መስራት እንዳለባቸው የገለፁት ርዕሰ መስተዳድሩ ፣የክልሉ መንግስት ለግሉ ባለሀብት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል ።
ይህንኑ በማጠናከር ሀገሪቱ ያቀደችውን ሁለንተናዊ ዕድገት በዘላቂነት ለማስቀጠል የተቀናጀ ትብብር ያስፈልጋል ብለዋል።
የክልሉ ኢንቨስትመንት ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ አፀደ አይዛ ፣በክልሉ በኢንቨስትመንት ፕሮጀክት በማህበራዊና በኢኮኖሚ ዜጎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተሰራ ነዉ ብለዋል።
በክልሉ አዳዲስ እንቨስትመንት በመሳብና በዘርፉ ዘመናዊ የአገልግሎት አሰጣጥ በመዘርጋት ዉጤታማነት ለማረጋገጥ እየተሰራ እንደሆነ ጠቁመዋል ።
በመድረኩም ርዕሰ መስተዳደር ጥላሁን ከበደ ፣የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም አልም ባለሀብቶች እየተሳተፉ ይገኛሉ ።
Copyrights 2021. . All Rights Reserved.
Developed by NATNAEL ABATE