• Call Us
  • +251..........

ሚሊየን ኮደርስ ስልጠና ዜጎች ከተለያዩ ሀገራት የርቀት ሥራ የሚያገኙበትን እድል እየፈጠረ ነው

የ5 ሚሊየን ኮደርስ ስልጠና ዜጎች ከተለያዩ ሀገራት የርቀት ሥራ የሚያገኙበትን እድል እየፈጠረ ነው 

የአምስት ሚሊየን ኮደርስ ስልጠና ኢትዮጵያዊያን በተለያዩ የዓለም ሀገራት የርቀት ስራ የሚያገኙበትን ዕድል እየፈጠረ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ፡፡

ኢትዮጵያ ከተለያዩ ሀገራት ጋር የሥራ ስምሪት ስምምነት መፈራረሟን የገለጹት ሚኒስትሯ÷ በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ለ344 ሺህ ዜጎች የውጭ ሀገር የሥራ እድል መፈጠሩን ጠቁመዋል፡፡

የ21ኛ ክፍለ ዘመን አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ የሚጠይቀውን ሥርዓተ ትምህርት በመቅረፅ ወጣቶች የዲጂታል ቴክኖሎጂ ክህሎት እንዲኖራቸው እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የአምስት ሚሊየን ኢትዮጵያን ኮደርስ ስልጠና የወጣቶችን የዲጂታል ቴክኖሎጂ አቅም በማላቅ ከተለያዩ ዓለማት የርቀት ሥራ እድል እንዲፈጠር አድረጓልም ነው ያሉት፡፡

በስልጠናው የሚሰጡ ኮርሶች ዓለም አቀፍ እውቅና የሚያስገኙ መሆናቸውን ገልጸው÷ 45 ሺህ ዜጎች በተለያዩ ሀገራት የርቀት ሥራ እንዲያገኙ ማገዙን ሚኒስትሯ ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

ከተለያዩ ሀገራት ኩባንያዎች ተጨማሪ ጥያቄ እየቀረበ መሆኑን አንስተው÷ ወጣቶች ሥራው የሚጠይቀውን የቴክኖሎጂ አቅም ገንብተው ወደ ሥራ መግባት ይችላሉ ብለዋል፡፡