የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ
የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የቀብር ሥነ ሥርዓት በዛሬው ዕለት በሮም በሚገኘው ሳንታ ማሪያ ማጆሬ ቤተ-ክርስትያን ተፈጽሟል፡፡
በቫቲካን ቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በተከናወነው የሽኝት መርሐ ግብር ላይ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን ጨምሮ የበርካታ ሀገራት መሪዎች መታደማቸው ተነግሯል፡፡
ከሀገራት መሪዎች በተጨማሪ የሃይማኖት መሪዎችና ከ250 ሺህ በላይ ምዕመናን መታደማቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ባደረባቸው ከፍተኛ የሳንባ ሕመም የሕክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ቆይተው ባሳለፍነው ሰኞ በ88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸው ይታወሳል፡፡
Copyrights 2021. . All Rights Reserved.
Developed by NATNAEL ABATE