• Call Us
  • +251..........

ባለፉት 7 የለዉጥ አመታት በሀገሪቱ መፍትሔ መሆን የሚችሉ ስኬቶች ተመዝግበዋል - አቶ ጥላሁን ከበደ

ባለፉት 7 የለዉጥ አመታት በሀገሪቱ መፍትሔ መሆን የሚችሉ ስኬቶች ተመዝግበዋል - አቶ ጥላሁን ከበደ 

መጋቢት 24/2017 ዓ.ም 

ባለፉት 7 የለዉጥ አመታት በሀገሪቱ መፍትሔ መሆን የሚችሉ ስኬቶች ተመዝግበዋል ሲሉ  የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ጥላሁን ከበደ ገልፀዋል ።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ሶዶ ከተማ የለዉጡን  7  አመታት የሚዘክር የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል ።

የድጋፍ ሰልፉ በኢትዮጵያ ባለፉት 7 አመታት የተመዘገቡ ስኬቶችን በቀጣይም በዘላቂነት ለማስቀጠል ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።

 የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በዚህ ወቅት ባለፉት 7 የለዉጡ አመታት በሀገሪቱ መፍትሔ መሆን የሚችሉ ስኬቶች የተመዘገቡበት መሆኑን ገልጸዋል ።

የለዉጡ መንግስት ባለፉት ሰባት አመታት በሀገሪቱ ያጋጠሙትን ዘርፈ ብዙ ፈተናዎችን በድል በመሻገር ዛሬ ላይ መድረሱን አቶ ጥላሁን ጠቅሰዋል ።

ለዉጡ በሀገሪቱ ለተገለሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዕድል የተሰጠበት ነዉ ሲሉ አቶ ጥላሁን ገልፀዋል ።

ኢትዮጵያ ያጋጠማትን ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ለመቅረፍ የተካሄደበት ሂደት የባለፉት ሰባት የለዉጡ  አመታት ለቀጣይ ስራ ስንቅ የሚሆን ነዉ ሲሉ አቶ ጥላሁን ጠቁመዋል ።

በሀገር በቀል የእርቅ ስርዓቶች ውስብስብ ችግሮችን ለመፍታት የተወሰዱት እርምጃዎች አንዱ ማሳያ መሆኑን ያስረዱት አቶ ጥላሁን ፣በዓሉ የህዳሴ ግድብ እየተጠናቀቀ ባለ ወቅት መከበሩ ልዩ ያደርጋል ብለዋል።

በቀጣይም  በክልሉ ያሉ ፀጋዎችን ከመደመር እሳቤ ጋር በማስተሳሰር የክልሉ ሆነ የሀገሪቱን ብልፅግና በማረጋገጥ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ የተሻለች ሀገር ለማድረግ እንደሚሰራ ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል ።

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ  ጴጥሮስ ወልደማርያም፣ባለፉት የለዉጥ ጉዞ በኢትዮጵያ ለዘመናት የቆዩ ውስብስብ ችግሮች የተቀረፉበት ነዉ ብለዋል።

በድጋፍ ሰልፉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ፣የክልሉ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ገብረመስቀል ጫላን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች እንዲሁም የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል።