የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ በመሆን የተሾሙት አቶ አባይነህ አበራ የስራ ርክክብ አደረጉ
መጋቢት 4/2017 ዓ.ም
የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ በመሆን የተሾሙት አቶ አባይነህ አበራ ከቀድሞው የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ሰናይት ሰሎሞን ጋር የስራ ርክክብ አድርገዋል።
የቀድሞው የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ሰናይት ሰሎሞን አዲሱን ኃላፊ ከተቋሙ ሰራተኞች ጋር በማስተዋወቅ በተቋሙ የስራ ዘርፎች ዙሪያ ዝርዝር ማብራሪያና ገለፃ አድርገዋል።
አዲስ ለተሾሙት የተቋሙ ኃላፊ መልካም የሥራ እና የስኬት ጊዜ እንዲሆንም ወ/ሮ ሰናይት ምኞታቸዉን ገልፀዋል።
አቶ አባይነህ አበራ ለተደረገላቸው አቀባበል ምስጋና አቅርበዉ ለቀድሞው የቢሮው ኃላፊ መልካም የስራ ጊዜን ተመኝተዋል።
የቢሮው ምክትል ኃላፊና የመንግስት መረጃ አስተዳደርና ዲጂታል ሚዲያ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ እታገኝ ኃ/ማርያም በበኩላቸው የቀድሞ ኃላፊ ወ/ሮ ሰናይት ክልሉ እንደ አዲስ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ያላቸውን አቅም ሳይሰስቱ በትጋት በመስራት አመርቂ ውጤት ማስመዝገባቸውን ተናግረዋል።
አዲስ የተሾሙትን ኃላፊ እንኳን ደህና መጡ በማለት ከመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች ጋር በመቀናጀት የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በጋራ እንደሚሰራ ወ/ሮ እታገኝ ገልፀዋል።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ የነበሩት ወ/ሮ ሰናይት ሰሎሞን የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ በመሆን ተሹመው ስራ መጀመራቸው ይታወቃል።
Copyrights 2021. . All Rights Reserved.
Developed by NATNAEL ABATE