• Call Us
  • +251..........

የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ አባልና የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕረዝዳንት አቶ አወል አብዲ የጌዴኦ መልከዓ ምድርን ጨምሮ የሌማት ትሩፋቶችንና አጠቃላይ በዞኑ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነዉ::

የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ አባልና የኦሮሚያ ክልል ክት ፕረዝዳንት አቶ አወል አብዲ የጌዴኦ መልከዓ ምድርን ጨምሮ የሌማት ትሩፋቶችንና አጠቃላይ በዞኑ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነዉ::

አቶ አወል ዲላ ከተማ ሲገቡ የዞኑና የዲላ ከተማ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና የከተማ ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል አድርገዉላቸዋል።

በጉብኝቱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ ግብርናና ገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ዉሃና ማዕድን ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር አክሊሉ አዳኝ ተገኝተዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚና የኦሮሚያ ክልል / ፕረዚዳንት አቶ አወል አብዲ በዞኑ ዛሬ በሚኖረው ቆይታቸው የጌዴኦ መልከዓ ምድርን ጨምሮ የሌማት ትሩፋቶችንና አጠቃላይ በዞኑ እየተከናወኑ ያሉትን የልማት ስራዎችን ይጎበኛሉ።

"ከተረጀነት ወደ ምርታማነት ለተሟላ ሀገራዊ ሉዓላዊነት እና ክብር" በሚል መሪ ቃል በነገው ዕለት በሚካሄደው ሀገራዊ መድረክ ሀገሪቱን ከተረጂነት ለማላቀቅ በሚደረገው ጥረት ዙሪያ ሰፊ ዉይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል።